ለአብን ጤንነት ኮሶ መጠጣት፤ ዶሮ ማታ እንላለን
ከኢያሱ ኤፍሬም ለንደን ፡ እለተ መጋቢት 11 2014 ፡ ተፃፋ 2022 ማርች 20, እሑድ፡ አንብቡት፡ አካፍሉት ፡ ተቹት
የአገሬ አዝማሪ እንዲህ ብሎ አዘመረ፡ ይመራል ይላሉ ኮሶ መጠጣት ፡ እሱስ የሚመረው ወዶ መለየት ፡ አዎ ወዶ መለየት የሚመር ይሆናል ነገር ግን መረረንም ጣፈጠንም ወዳጅ ወዳጅ ካልሆነ መልካም ነው በተጨማሪም በሆዳችን የተፈጠረውን ተውሳክ ለማሶገድ እና በጤና ለመኖር ከፈለግን ኮሶ መጠጣት ውዴታ ሳይሆን ግዴታ ነው፡ በአንጀታችን ውስጥ የተፈጠረ ተውሳክን በጊዜ ካላስወገድነው ተውሳኩ ሌላ አካላችን ተዛምቶ ለእልፈት ይዳርገናል፡ አብን ምርጫ የለውም ለመዳን መራራውን ኮሶ ከመጠታት ውጭ ፡ ከወዳጅ መለያየት ቢከፋም መለያይተ ግድ ነው
አማራ በብሔር ለመደራጀት ያደረገው ትግል በጠላቶቹ ሴራ እና አማራው ለኢትዮጵያዊነቱ ቅድሚያ በመስጠቱ ምክንያት ከፕሮፌስር አስራት ወልደየስ የመላው አማራ ድርጅት በኋላ ትርጉም ያለው የአማራ ፖለቲካዊ ስብስብ ሊፈጠር አልቻለም ነበር፡፡ በተጨማሪም በአማራ ጎሮሮ ውስጥ የተሸነቀረው ብአዴን የተባለው አጥንት የአማራን ስቃይ እና ሞት ለማፋጠን ከአማራ ጠላቶች ጋራ በትጋት እንደሚሰራ የአደባባይ ሚስጢር ነው፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ከአራት አመት በፊት የወያኔን ከአራት ኪሎ ስንብት ተከትሎ በተፈጠረው መልካም አጋጣሚ የአማራ ወጣቶች ተሰባስበው አብን ፈጥረዋል ወይም እንዲፈጥሩ ተደርጓል፡፡
በአብን አፈጣጠር ዙሪያ የሚነሱ ብዙ፣ ያልጠሩ እና የሚያጠራጥሩ ጉዳዮች አሉ፡፡ ኦሪት ዘፍጥረተ አብን በግልፅ ያልተፃፈ መፅሐፍ ነው ፡ ከፈጣሪው እና ከተፈጠረው ውጭ የሚያውቀው የለም፡፡ እንዲህም የሚሉ አሉ፡፡ ቃልም ነበረ ቃሉም ብአዴን ነው ብአዴንም በአምሳሉ ፍጡር ሊፈጥር ወደደ ካድሬም ስብስቦ እፍ ብሎ አብን ሰራው ፡፡ አብንም በገነተ አማራ ይኖር ነበረ ፡ ሰይጣንም አብይን ተመስሎ አሳሳተው አብን ተጠግቶ የስልጣንን ፍሬ ብላ አለው ፡ አብንም ሃጤያት መስራቱን አወቀ፡ ከገነተ አማራ ተባረረ፡፡ አብንም ከገነተ አማራ ሲባረር ወደ አባቱ ወደ ፈጣሪው ብአዴን ሄደ፡፡ ይህን በተመለከተ አንድ ወዳጄ አብን በተፈጠረ ማግስት የነገረኝን ሐሜት ነው ብዬ እንድተወው ብገደድም አሁን ግን ለማመን ዳር ዳር እያለኝ ነው፡፡ በተለይ የአብን ምስራታ የነ ደመቀ መኮንን እጅ አለበት የሚለውን ማመን በወቅቱ አስቸግሮኝ ነበር፡፡ አሁን ግን ጠርጥር ጎንፎ ውስጥ አለ ስንጥር እንድል አድርጎኛል፡
በሌላም በኩል ፖለቲካን የእለት ተግባሩ እንደ አደረገ ግለሰብ ከሚታማማበት አፈጣጠሩ ውጭ አብን ብዙ እንዳላምነው የሚያደረጉ እና በአብን ላይ ጥርጣሪ አንዲፈጥሩብኝ ያደረጉ ምክናታዊ ክስተቶች ነበሩ፡፡ ይህን ጉዳይ በአደባባይ ለማንሳት እና ለመወያየት በወቅቱ በተፈጠረው የአብን ቅቡልነት እና የፖለቲካ ድባብ (Euphoria) አይፈቅድም ነበር፡፡ በወቅቱ አብንን መውቀስ ማለት እራስን በድንጋይ ማሶገር ማለት ነበር ፡፡ እኔ ደግሞ እስጢፋኖስ አይደለሁም፡፡ ያለ መታደል ሆኖ በማሕበርሰባችን ውስጥ ምክናታዊ ሙግት የማይቀናቸው ሰዎች ቁጥር ቀላል አይደልም፡፡ ለማናቸውም ትምህርት ይሆን ዘንድ በአብን ላይ የነበርኝን ምክናታዊ ጥርጣሬ ( Reservation) እንደሚከተለው አቀርባለሁ፡ ተከተሉኝ፡፡
አንደኛ ጥርጣሬ ( Reservation)፡ አብን በአማራው ሕዝብ ውስጥ ስራ አለመስራቱ ነው፡፡ ሁላችንም እንደምናቀው አብዛኛው የአማራ ማህበረስብ ገብሬ ነው፡፡ የአማራን ብሶት እና በደል አዳምጣለሁ የሚል የፖለቲካ ድርጅት መጀመሪያ የቤት ስራው መሆን ያለበት አብዛኛው ሕዝብ ላይ ነው ፡፡ እሱም ገበሬው ነው፡፡ 80% የሚሆነውን ሕዝብ ሳታደራጅ ሳታነቃ እና ከጎንህ ሳታስለፍ እሱን እወክለዋለሁ በሱም ስም ለስልጣን እበቃልሁ ማለት የመጀመሪያ የፖለቲካ ስህተት ነው፡፡ አንድ ወዳጄ በሰሜን ጎንደር ገጠራማ ቦታ የሚኖሩትን ዘምዶቹን ስለ አብን ጠይቋቸው የስጡት መልስ ለአብነት የሚቀርብ ነው፡ አብን ስለሚባል ድርጅት ታውቃላችሁ ተብለው ሲጠየቁ ፡ መልሳቸው እሷ ማን ነች እኛ ምናውቀው ብልፅግናን ነው ፡፡ ብልፅግና ታሻግረናለች በለውት እርፍ፡፡ ይህን እንግዲህ በሰፊው የአማራ ሕዝብ ውስጥ አባዙት ፡፡ ይህንንም በማድረጋቸው አብንኖች ከሰፌው የአማራ ሕዝብ ተነጥለው የከተማ ወይም የዲኦደራንት አብዮተኞች ( Deodorant Revolutionaries) ሆነ ነው የተከስቱት፡፡
ሁለተኛ ጥርጣሬ ( Reservation) ፡ የአመራሩ የፆታ ስብጥር ነው፡፡ በቲውተር መደቤ የማዋያት አንዲት ወጣት የአብን መስራች መሆኗ ብትነግረኝም በአብን የላይኛው አመራር አንድም ሴት አለማየቴ ስለ አብንኖች ያለኝን ጥራጣሬ አሳድጎታል፡፡ በአብን አመራር ውስት ሴቶች አለምኖራቸው የአጋጣሚ ጉዳይ ነው ብዬ አላምንም ፡ ሆን ተብሎ የተደረግ እንጂ ፡፡ ደርግ ምስጋና ይግባው እና ስለ ሴቶች እኩልነት አስተምሮ ሄዷል ( የጎጃሙ ኦምጫባው ያለው እንደተጠበቀ ሆኖ)፡፡ አሁን ባለንበት ሰአት ሰለሴቶች የፖለቲካዊ የማህበራዊ የኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ አስፈላጊነት የምናወራበት ወቅት አይደለም፡፡ ይህ አለም ያወቀው ፀሐይ የሞቀው ጉዳይ ነው፡ እንኳን ፖለቲካኛ የምንባል ሰዎች አይደለንም ተራው ሰው የሚያውቀው እውነታ ነው ፡፡ አብን አመራር ግን ከ50% የሚሆኑትን ሴቶች በማይወክል መልኩ መደራጀቱ ለመዳባደብ የተደራጁ የሰፈር ጎረምሶች እንጂ የፖለቲካ አመራሮች አያስመስላቸውም፡፡ ይህ ደግሞ ምንጩ በአብን አመራር ውስጥ የተሰባሰቡት ሰዎች ስነ ልቦና ነው፡፡ አብይ በእዚህ መልኩ ተሽሎ መገኘቱ ይሰመረበት፡፡
ሶስተኛ ጥርጣሬ (Reservation) ፡ አብንኖች እንደ ፖለቲካ ድርጅት እራሳቸው ከአባሎቻቸው ፡ ከሕዝብ ጋራ የሚገናኙበት መንገድ በአግባቡ አለመዘርጋታቸው ነው፡፡ ይህም ሚዲያ ነው ፡፡ አንድ የፖለቲካ ድርጅት እወክለዋለሁ የሚለውን ምሕበረስብ በተለያየ መንገድ መድረስ አለብት ፡ ከእዚህም አንዱ መንገድ በየጊዜው ( በሳምንት ሊሆን ይችላል) በሚወጡ ፅሁፎች ነው ፡፡ አብን ግን እንደ መስከረም ወፍ አስቸጋሪ እና የማያነካካ ክስተቶችን ብቻ ተከትሎ አልኩኝ ለማለት በሚመስል መልኩ መግለጫ ቢጤ ጣል ያደርጋል፡፡ የአማራ ሕዝብ በየቀኑ በሚባል መልኩ እየተገደለ ፡ እየተፋናቀለ፡ መካራ እየደረሰበት ባለበት ወቅት የአብን አቋም ለሕዝን ግልፅ አይደረግም፡ ይህ የሚያሳየው የአብን አድር ባይነት ነው፡፡ በሌላኛው ወገን በያንዳዷ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሲያወጡ ማብራሪያ ሲያቀርቡ አብን ግን አሽዋ ውስጥ አንግቷን እንደ ቀበረች ሶጎን ሆኖ ነው የተገኘው፡ አብን ሕዝባዊ ከሆነ እና እና የሕዝብን ብሶት ለማሰማት ከፈለገ በየሳምቱም ወይም በየእለቱም የሚዘጋጅ የራሱ ድርሳን ( Communiqué ) ሊኖረው ይገባ ነበር፡፡
አራተኛ ጥርጣሬ (Reservation) ፡ አብን ከአገር ውጭ ካለው አማራ ጋራ ያለው ግንኙነት ነው፡፡ በብዙ መልኩ በውጭ ያለው አማራ ለአብን ከፍተኛ አቅም ሊሆነው እንደሚችል ጥረጠር የለውም ፡፡ እነ ግንቦት ሰባትን፣ አርበኞችን እና ኢሳትን ተሽክሞ መኖሩ መዘንጋት የለበትም ( ጠላቶቹን)፡፡ ነገር ግን እኔ ባለኝ እውቀት እና መረጃ መሰረት አብን ይህንን አቅም በአግባቡ አልተጠቀመበትም፡፡ ሲጀመር የውጭ አደረጃጀት አልፈጠረም ፡አብዛኛ በውጭ ያለው አማራ አብንን የሚደግፈው እራሱ በፈጠርው አደረጃጀት ነው ፡፡ ለዚህም ማሳያ ባለፈው ምርጫ ወቅት አብን የገንዝብ እጥረት ስለገጠመው በየአቅታጫው ያደረገው የገንዘብ ርዳታ አድርጉልኝ ጥያቄ ነው ፡፡ እኔም ከቋቱ ጠብ አድርጊያለሁ፡፡ እዚህ ላይ መጠየቁ ክፋት አለው እያልኩኝ አይደለም ፡፡ ነገር ግን ሂዳቱ የሚያሳየው አብን በውጭ አገር የተደራጃ መዋቅር እንደሌላው ነው፡፡ ቢኖረው ኖሮ አባሎች በየወሩ የሚሰበስቡት ገንዝብ በቀላሉ ሊደጎም ይቻል ነበር ፡ ለምሳሌ በውጭ ካለው አማራ 50 ሺ አባሎች ቢኖሩት እና እያዳዳቸው በወር 5 ዶላር ቢያዋጡ በወር 250 ሺ ዲላር ማስባሰብ በተቻለ ነበር ይህን በአመት ቢሰላ 3 ሚሊዮን ዶላር ማለት ነው፡፡ ይህን በ50 ብር ብንመታው 15 ሚሊዮን ማለት ነው፡፡ ከገንዝቡም በተጨማሪም ውጭ የሚኖረው አማራ በቁስም ሆን በእውቀት ( እኛ ብቻ አዋቂዎች ነን ካላሉ በቀር) ከፍተኛ ግብአት ሊያገኙ ይችሉ ነበር ፡፡ ነገር ግን ከጅምሩ አመሰራረታቸው የጠራ ባለመሆኑ አብን የውጩን ኃይል በሩቁ አድርጎታል የሚል ግምት አለኝ፡፡
ከእዚህ ቀደም አብን በእርዱን ( Gofundme) መድረክ ገንዝብ ለማሰባሰብ ተሞክሮ ገንዝቡን በአደራ የሰበሰቡት ግልስቦች ክህደት እንደፈፀሙ ተሰምቷል፡፡ ይህ ክስተት የግለሰቦቹ ከዳተኝነት እና ሌብነት እንደ ተጠበቀ ሆኖ አብን እንደ ሕዝባዊ ፖለቲካ ድርጅት አለመስራቱን ነው የሚያሳየው ፡፡ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ጥንካሬው የሚለካው በአባሎቹ ታማኝነት እና ቁርጠኝነት፡ እና በፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ባላቸው ሙሉ ተሳትፎ ወይም የመምረጥ እና የመመረጥ፡ የመብት እና የግዴታ ተግባራትን ተግባራዊ ሲያደርግ ነው፡፡ አብን የመንደር ስራ በመስራቱ ይህን የማይሰበር የፖለቲካ ሕግ (cardinal rule) የሰበረ ይመስለኛል፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት የአብን አመራ ሕዝባዊ አለመሆኑ እና ከተጠያቂነት ለመራቅ የሚል ጠንካራ እምነት አለኝ፡፡
አምስተኛ ጥርጣሬ (Reservation) ፡ የአመራሩ አመራረጥ እና ስብጥር ነው፡፡ በርግጥ የአመራር አመራረጥ እና ምልመላ ከባዱ እና አስቸጋሪ ጉዳይ ነው፡፡ በአንድ በኩል አመራር ሲመረጥ መቀመጥ ያለባቸው መስፋርቶች አሉ፡ አንዱ የመሪነት አቅም (leadership skills)፡ ቅቡልነት ፡ አንፅራዊ እውቀት ( ትምህርት ዝግጅት ) ፡፡ ለአላማው የቆመ ፤ ፅኑ፡ በትግል የተፈተነ ፡ በስነ ምግባር የተሞላ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ነገር ግን እንዚህን ሁሉ አሟልቶ መገኘት ከባድ ነገር ነው ፡፡ በአብዛኛው አመራረጡም ሆነ የተመረጡ መስፈርቶች እርስ በእርሳቸው የሚጣረሱ ወይም catch 22 ሁኔታ የሚፈጥሩ ናቸው (ይህን ለአሁኑ አልሄድበትም)፡፡ ሁሉንም መስፋርቶች አሟልተው ተመረጡ የሚባሉ አመራሮች ነገ በተግባር ሲፈተኑ እውነተኛ ማንነታቸው ሌላ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ ይህ በፖለቲካ ውስጥ ሊያጋጥም የሚችል እና የፖለቲካ ከፍተኛው ተግዳሮትም ነው፡፡
በሌላ በኩል የማሕብረስባችን ማሕበራዊ የኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ እድገቱ በጉልተኛ ስርአት ( Feudal System) ተቀርቅሮ (stagnant) በመቅረቱ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ አሁንም ቢሆን ማሕበረስባችን የጉልተኛው ስራት ስነ ልቦና እስረኛ እንዲሆን አድርጎታል፡፡ አብንም ከእዚህ ማሕበረስብ የወጣ በመሆኑ አመራር አመራረጥ ሂደቱ ከጉልተኛው ስርአት ስነ ልቦና የፈለቀ ነው የሚል ግምት (hypothesis) አለኝ፡ ለእዚህም እንደ ማሳያ የአብን የመጀመሪያው እና ቀጣዩን መሪ አመራረጥ ብንፈትሽ ያቀረብኩትን መላ ምት እውነት ያደርገዋል ፡፡ የመጀመሪያወ የአብን መሪ ዶክተር (ደሳለኝ ጫኔ) ነበር የተካወ እረዳት ፕሮፌሰር ( በለጠ ሞላ ) ነው፡፡ እነዚህን ሁለት አመራሮች ከመሪነት መስፈርት ውስጥ አስገብተን ብንመዝናቸው 50/100 ነጥብ ማምጣታቸውን እጠራጠራለሁ፡፡ በተለይ እረዳት ፕሮፌሰር ሞላ፡፡ ምክንያቱም ሌላውን ትንታኔ ሳያስፈልገን ዛሬ አብን የደረስበትን ቁመና አይተን አሳማኝ ወደ ሆነ ድምዳሜ ላይ መድረስ እንችላለን፡፡ ይህን መከራከሪያ ነጥብ በእውቀት ማገዝ የሚፈልግ ሰው ካለ Emotional Intelligence: Why It Can Matter More Than IQ. By Daniel Goleman የሚለውን መፅሀፍ ቢያነበው እመክራለሁ (ዶክቶሮቻችን ተነቀፉ እንዳትሉ) በተጨማሪም Intellectuals and Society by Thomas Sowell. መመለክቱ መልካም ነው፡፡ ወይም በመፀሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለተጠቀሱት ፈሪሳዊያን ማንበቡ ጠቃሚ ነው፡፡ የፈሪሳውያን 50 ምልክቶች
እንዚህ ሰዎች ወደ አመራር የመጡት አበይት ምክንያት ለመሪነት በተቀመጡት መስፋርቶች አሟልተው ካልሆነ ወደ አመራር ሊመጡበት የቻሉበትን ምክንያት በጉልተኛው ስርአት የስነ ልቦና ውቅር ውስጥ እናገኘዋልን ፡፡ የጥንቶቹ ቀኝ አዝማችች፣ ደጅ አዝማቾች እና ፊታውራሪዎችን ማእረጎች በዛሬዎቹ ዶክተሮች እና ፕሮፌሰሮች ተተክተው እናገኛቸዋልን፡፡ ስለሆነም ለመሪነት ከስራ ይልቅ ስም እና መአረግ ቅድሚያ እንሰጣለን ማለት ነው፡፡ በገሃድም እንደሚታየው በኢትዮጵያ የትምህርት መአረጎች በቀላሉ ወደ ስልጣን መወጣጫ ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ አብይም ከስምተኛ ከፍል ዘሎ ዶክተር የተባለበት ስሌት ከእዚህ የተለየ አይደለም፡፡ በብአዴን መአከላዊ አመራር ውስጥ ከአስር በላይ የዶክትሬት መእረግ ያላቸው አስተውያለሁ፡ ነገር ግን አስር የዲክትሬት ተመራቂዎችን አንድ የስምንተኛ ክፍል ወይም አባይ ተመራቂ ቁጭ ብድግ ያደርጋቸዋል፡፡
የአብን አመራር በተመለከተ ከሁለቱ ይልቅ ፊት ለፊት በመጋፈጥ የሚታወቀው ክርስቲያ ታደለ የተሻለ አመራር ሊስጥ ይችላል የሚል ግምት አለኝ ፡፡ ግን እሱ ዶክተር ወይ ፕሮፌሰር አይደልም፡፡ እንግዲህ ይህ ቀመር ነው አማራን እና አብንን የስነ ልቦና ሰለባዎች እንዲሆኑ ያደርጋቸው ፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ባሕል ከ66ዋቹ አብዮተኞች የተወሰደም በሽታም ነው፡፡ በቀድሞው ቀ/ኃ/ሥ/ ዩንቨርስቲ የነበሩት አብዮተኞች የመሪነቱን ቦታ የሚይዙት ባላቸው የትምህርት ውጤት ነው ፡፡ ሰቃይ ተማሪ መሪ መሆን አለበት የሚል ያልተፀፋ መመሪያ ነበራቸው፡፡ ደርግም ስልጣን በያዘ ማግስት የሚተችበት ትልቁ ነጥብ ወቴ ( ወታደር) ምን ያውቅና የሚል ነበር፡፡ ያ ማለት የተማርነው እኛ ነን እና አገርም መምራት ያለብን እኛ ነን አይነት ፖለቲካ ጨዋት ፡፡ ውጤቱን አይተነዋል ፡፡
ለማጠቃለል፡ አብን ከአመሰራረቱ ጀምሮ ችግር የነበረበት ድርጅት እንደነበር ሲነግር ቆይቷል ፡፡ ማናቸውም ድርጅት የራሱ ችግር አለው ያለ ችግር የተፈጠረ እና የሚኖር ድርጅት የለም ፡፡ ነገር ግን አንድ ድርጀት ከተነሳበት አላማ እና መሰረት ውጭ ከሄደ ወይም ከፈፀመ ያ ደርጅት ችግር ብቻ ሳይሆን ያለው በሽታም ጭምር ነው፡፡ አንዳድ በሽታዎች የማይድኑ ካንስሮች ናቸው አንዳንድ በሽታዎች በአገር ባሕል መድሐኒት ወይም ትንሽ ወጌሻ የሚድኑ ይሆናሉ፡፡ ለመዳን ግን መታመምን ማማን ያስፋለጋል ለመዳን መድሐኒቱን መውስድ ግድ ይላል፡፡ የአብን ትልቁ የፖለቲካ ሃጢያት ወይም ስህተት እወክለዋልሁ ብሎ የተነሳውን ሕዝብ ለማይወከለው ኃይል አሳልፎ መስጠቱ ወይም በዲናር መሸጡ ነው፡፡ ይህ የግለስብ ጉዳይ አይደለም ፡ አሳ ከአናቱ ይገማል እንደተባለው አብን የተበላሸው ከአናቱ ነው፡፡ በማናቸውም የፖለቲካ ሳይንስ (ጥበብ) ሊታገዝ ወይም ሊታረም የማይችል ስህተት ነው፡፡ ከውሻ ጋ የተኛ ቅማል ይዞ ይነሳል ይባላል ፡፡ ከአማራ አራጅ ጋራ ተኝተህ የዘህ የምትነሳው ካራ መሆኑን እወቅ፡፡
አሳ አስጋሪዎች በመጠንቆ ላይ ትንሽ ትል አስረው ወደ ሐይቁ ልከው አሳውን በመጥንቆ አንደሚይዙት ሁሉ አብይ አህመድ ለአብን አመራሮች በጋራ በመስራት ስም በመጠንቆ ላይ ትንሽ ስጋ ( ስልጣን እና ደሞዝ) አስቅምጦ ከባሕሩ( ከሕዝብ) ነጥሉ አመራሮችን አዋጣቸው አጠመዳቸው፡፡ አመራሩ የተቀመጠበት ስልጣን እና ወንበር ሲመቸው እና ሲደላደል እንዲሁም ጥቅሙ እንደ ቢርቢራ ቢያስከረው “የአማራ ብሔርተኝተ ታክቲካል እንጂ ያመንበት የትግል ስልት አደረጃጀት አይደለም” ማለት ጀመረ፡፡ አሁን እነዚህ አመራሮች ለአብን ሆነ ለአማራ ሕዝብ እንደ ኮሶ ትል የሚታዩ እንጂ እንደ አንድ አካል ወይም እንደ ሕዝብ መተፈሻ ሳምባ እንደ ትርታ አድማጭ ልብ ሆነው የሚቆጠሩ አይደሉም፡ ስለሆነም የኮሶን ትል ማሶገጃው መንገዱ ቢመርም ኮሶን በጥብጦ መጠጣት እና ኮስን ወደ ቦታው መጣል ነው፡፡ ስለሆነም የተቀረው የአብን አባልም ሆነ አመራር በአንድ ሙሉ ሺሪሚሪ ጣሳ ኮሶ መጠጫው አሁን ነው፡፡ ዶክ ደሳለኝ ጫኔ እንዳለው “ትግል የጀመርነው ትናንት የታገልናቸውን ለመሆን አይደልም፡፡ የአማራ ሕዝብ የመረጠኝ ከብአዴን ጫንቃ እንድናላቅቀው እንጂ.... እንዲሁም ዶ/ር ቴዎድሮስ ሀይለማርያም እንዳለው “እኔ አብንን የተቀላቀልኩት የአማራን ህዝብ ችግር ለማቃለል እንጂ ድህነቴን ለማራገፍና ኑሮየን ለማሻሻል አይደለም…..” ያሉት በራስ ዳሽን ተ