የገዱ እና ዣንጥራር የአሉ ፖለቲካ፡ ለኑዛዜ ወይ ለሱባኤ

አንጀቴ ተቆርጦ ከሆዴ ከወጣ ከንግዲህ ሃኪሙ ምን ሊፈጥም መጣ

ከኢያሱ ኤፍሬም ፡ ለንደን መጋቢት 2 20142022 ማርች 11, ዓርብንቃ ዐማራ አምብቡት ፡ አጋሩት ፡ ተቹት ማማ

የባለ ቅኔው ስንኝ

ስሟን የማላስታውሰው አቀንቃኝ ከላይ የጠቀስኩን ስንኝ የያዘ የፍቅር ቅኒ እስታቆረቁር ስምቻለሁ ፡፡ አዎ ከቅረኛዋ ጋራ ከተቆራረጠች በኋላ ሽማግሌው እና አማላጅ ቢመጣ ምን ሊፈይድ ፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ተወዳጁ ልጃችን ሙሉቀን መለሰም ምነው ከረፈደ በሚለው ዜማው የሚቅጥለውን ስንኞች አስደምጦናል ፡፡ የሰራሽኝ በደል ሥሩ ከሰደደ ፡ ይቅርታሽ ደረሽኝ መነው ከረፈደ፡፡ ብሎ ቀኑ ሲረዝምብሽ እኔን ካላየሽን ፡ ጭንቀት ሲበዛብሽ ለኔ ካልነገርሽን ይላል ፡፡ ይህ ጊዜ የማይሽረው የሙሉቀን ስራን ዛሬ በማህበራዊ ዜና አውታር ከሚዘዋወረው አሉ ከሚለው ዜና ጋር አስማማቼ ለጠቀምበት ወደድኩኝ፡፡  ተከተሉኛማ

የሰራሽኝ በደል ሥሩ ከሰደደ
ይቅርታሽ ደረስኝ ምነው ከረፈደ

 

ለይቅርታው ጊዜ አልዘገየሽም ወይ
ያፈቀረ ጊዜው አይረዝምበትም ወይ

 

ሆነሽ በደለኛ ጣል ጣል አድርገሺኝ
ዛሬ ከተሰማሽ እኔን የሰራሺኝ

 

ልክ እንደቸልታሽ እንደኩያሽ በደል
ምነው አልነገርሺኝ ለጥፋትሽ ምክንያት

 

ከዛሬ ከነገ ሲጠብቅሽ ልቤ
ትመጣለች ብዬ ወስኜ በሀሳቤ

 

አልረፈደብሽም አዬ አልዘገየሽም ወይ
ለወደደ ጊዜ ፋታ ይሰጣል ወይ

 

የአሉ መንደር ከንቱ ጩኽት

አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንዲህ ብለው ተናግረዋል አሉ፡ "በቀረችኝ የህይወት ዘመኔ ህዝቤን ለዳግም ባርነት አልዳርግም! ፋኖ ትጥቅ ይፍታ የሚለውን የብልፅግናን አካሄድ አጥብቄ እቃወማለሁ:: ፋኖ የሀገር ዳር ደንበር ዘብ እንጅ የአሸባሪ ተግባር የሚፈፅም ቡድን አይደለም! ሁሉም አማራ ደግሞ ፋኖ ነው"  ይሄኔ ነው ምነው ከረፈደ ማንጎራጎር፡፡  የቀራቸው ዘመን ምን ያህል ነው? ወይስ ገና ከአማራ የሚፈለጉት ነገር አለ?   

ሌላም ብአዴንናዊ አቶ ፀጋ አራጌ እንዲህ አሉ፡ በአማራ ደም የሚበለፅግ ፓርቲም፣ የምትበለፅግ ሀገርም አንፈልግም ያሉት አቶ ፀጋ አራጌ ክልላዊ ፓርቲያችንን በማክሰም ሀገራዊ የሆነውን ብልፅግና ፓርቲ የመሰረት ነው ለህዝባችን ተጠቃሚነት ብቻ ስንል ነው። እንደ ሀገር ባለፉት 30 አመታት የፖለቲካ ውክልና የተነፈገውን የአማራ ህዝብ ሀገር እንዳለው፣ ወገን እንዳለው ለማሳየት ነው”

ሌላው ደገሞ አቶ ቀለምወርቅ ምህረቴ ደግሞ እንዲህ አሉ አሉ፡  “ህወሀት ቀድሞም ቢሆን ተደቁሷል፤ደቋል፤ዱቄት ሆኗል ተበትኗል፤እየተባለ ይህንን ያክል በአማራ ላይ ጉዳት ሲያደርስ የብሔራዊ መረጃ እና ደህንነት ምን እየሰራ ነበር፡፡ከነመኖሩም እጠራጠራለሁ፡፡የነስብሀት ነጋ መፈታትም የሚያሳየዉ የመንግስትን ድክመትና መንኮታኮት ነዉ” ብለዋል፡፡ ጥያቄ እርሶ እራሶ ምን እየሰሩ ነበር?

የከንቲባ አዳነች አቤቤ ዣንጥላ ያዥ አቶ ዣንጥራር አባይ እሳቸውም እንዲህ አሉ አሉ  “በህወሀት ኢህዴግ ዘመን ዜጎች አረንጓዴ፤ቢጫ እና ቀዩን ሰንደቅ አላማ ይዘዉ ሲወጡ ይታሰሩ እና ይገደሉ ነበር፡፡ይህ አሁንም በብልፅግናም ቀጥሏል፡፡ አረንጓዴ፤ቢጫ እና ቀዩን ሰንደቅ አላማ ከሚይዙት ሰዎች ጋርም ተገናኝታችኋል እየተባልን እየተገመገምንና እየተተቸን ነዉ ሲሉ ጠንከር ያለ ሀሳብ አንስተዋል፡፡” ጥሎ መውጣጥ የሚባል ነገር አለ፡

የአሉ አሉ መንደር ፖለቲካ በወፍ በረር ሲፈትሽ

ዛሪ በአሉ አሉ መስመር የተሰለፉ የብአዴን አመራሮች ቆጥራቸው በዛ ያለ መጥቷል ፡፡ ይህ ግን አዲስ አይደለም  አቶ ዮሃንስ ቧ ያለው ፡ ቧ ብለዋል ከተባለ አመታት ተቆጠረዋል ፡፡ ቧ ግን ሟ ሆና ነው የቀረው፡፡ እንዲያውም በአዲስ ሹመት ከብረው ተቀምተዋል፡፡  እንደ እውነቱ ለመናገር እስካሁን በጆሮቴ የሰማኋቸው እና በቃላቸው  የኖሩ እውነተኛ የአማራ  ሁለት ሰዎች  ነበሩ እንሱም ፡  ጀነራል አሳምነው እና ዶክ አምባቸው ናቸው  ነፍሳቸውን በአፀደ ገነት ያኑረው እና  ዶክ አምባቸው  በግምባሬ እንጂ በጀርባዬ ጥይት አይመታኝም ከሚል ማህበረስብ ነው የተወለድኩት ሲል የተናገረው ተንቢት ሆኖ በግንባሩ ጥይት ገብቶ ተሰዋ፡ ቀጥሉም ጀነራል አሳምነው እንዲሁ አማራ ተክቧል እንዳለው እሱ እራሱ ተከቦ በወረብሎች ተገደል፡፡ በአሁንም ወቅት በክፉ ጊዜ ጠረተው የልዩ ኃይል  አዛዥ ያደረጉት እና በቅርቡ ከአዛዥነት አንስተው ወንበር እንዲያሞቅላቸው የፈለጉት ጀነራል ተፈራ ማሞ ቁርጥ የአማራ ለጅ መሆኑን በተግባር አሳይቷል ፡፡ የጀነራሉን ተምሳሌነት ወደ በኋላ ተመለሼ እመጣበታሉ፡፡

ማሳሰቢያ ፡ በሰኔ 15 ክስተት ላይ የጎራ መከፋፋል እንዳለ አውቃለሁ ነገር ግን የኔ እይታ የተመሰረተው የሕግ መሰረታዊ መርሆ ላይ እንደሆነ ይታውቀለኝ፡ ጥፋተኛ ሆነ እስኪፈረድብህ ድርሰ ንፅህ ሰው ነህ የሚለው መርሆ የምገዛበት መርሆ ነው   innocent until proven guilty' እስከማቀው ድረስ የሁለቱም ሰዎች ሆኑ በወቅቱ በተከሰተው ክስተት ሕይወታቸውን ላጡ ፍትህ አልተሰጥም፡፡ በቅርቡ በጉዳዩ ላይ እጃቸው አለበት በተባሉት ላይ ፍርድ ቤት ብያኔ አተላላፏል ፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ የፍርድ ሂዳቱ ከዝንጀሮ ሽንጎ kangaroo court ለይቼ አላየውም፡፡ ጉዳዩ መታየት የነበረበት በሕዝባዊ ሽንጎ  Public inquiries ነበር )፡ ነገሩ፡ ዳኛው ዝንጀሮ ፡ ፍርድ ቤቱ ገደል ከምን ላይ ቆሞ ይነገራል በደል መሆኑ ነው፡፡  

አጠቃላይ የብአዴን ስብስብ ላለፉት 30 አመታት ያለ አንዳች ይሉኝታ ፣ ፀፀት እና ቅሬታ ከአለቆቻቸው የተሰጣቸው ትዛዝ የአስፈፀሚነት ተግባር ያለ ጥያቄ ተቀብለው የአማራን ሕዝብ ሲገሉት፣ ሲያስገድሉት፣ ሲያሳድዱት፡ ሲያደኽዩት ፡ ሲመዘብሩት ፡ ሲያውርዱት የኖሩ ናቸው፡፡ከጳጳሱ ቄሱ እንዲሉ የብአዴን አማራሮች ከሚታወቁበት ድርጊታቸው አንዱ ከወያኔው ሆነ ከኦሮሙማ ብሰው እና በለጠው አለቆቻቸውን ለማስደሰት በአማራ ሕዝብ ላይ ያለ ትሉኝታ መዝመታቸው እና ማስታውካቸው ነው፡፡

ገና ከጅምሩ ይህን ነፍጠኛ አማራ በለው ያለው የኢሕዴንኑ መሬ ታምራት ላይኔ ነበረ ፡፡ ከአህያ የዋልች ጊደር ፈስ ተምራ መጣች እንዲሉ በታምራት ላይኔ እና በበረከት ስምኦን ስሪት የተመረቱት የብአዴን ስዎች  አማራን የምንታገለው ሕዝብ እንጂ የምንታገልለት አይደለም ብለው ተነሱ፡፡ አማራ የትምክህት ..... እያጠባጠበ በባዶ እግሩ እየሄደ ያለው በብአዴን ውስጥ ሙሁራዊ መአረግ ያለው ሰው ነው ፡፡ ያ ብቻ አይደለም ፡፡ የአማራን ሕዝብ በድለናል  አጥፍተናል ተላላኪ ነበርን ማሩን ካሉ በኋላ፡ በአማራ ወጣቶች ደም መስዋትነት የመጣውን ለውጥ አውጥተው ቱቦ ውስጥ  የጣሉት እንዚሁ ብአዴኖች ናቸው፡፡  አቶ ገዱ እኛ የታገልነው ለስልጣን አይደለም ብለው እርፍ አሉ፡፡ ታዲያ የሰንበቴ እቁብ ሊጠጡ ነበር ወይ ኦሮአማራን የመሰርቱት ብሎ የጠየቀም አንዳችም ሰው አለነበረም ፡፡ ያወ በአማራ ወግ እና ደምብ ሁሉም እያጎትመተ ዝም አለ፡፡ ጉድ ሳይስሙ መስከርም አጠባም አይነት ነገር መሆኑ ነው፡፡

ምነው በእንቁላሉ በቀጣሽን እንዲሉ ገዱ እና ባልደረቦቻቸው ሆ ብሎ ወደ ስልጣን ያወጣቸውን ሕዝብ ዳግመኛ  ክደው የኦሮሙማ ውክልና ተቀብለው  በአማራ ሕዝብ ላይ ሰይፋቸውን መዘዙ፡፡ የሰኔ 15ቱን ክስተት ተከትሎ የአማራን ፋኖ እያሳደዱ በእናቱ ደጅ ደፉት ፡፡ ተመስገን ጥሩነህ ዳግማዊ መላኩ ተፈራ ሆኖ ተከሰተ ፡፡ ለእኩይ ስራውም በአለቃው ሹመት ተቸረ፡፡ አማራ በአብይ መራሹ መንግስት በሚታገዘው የአረመኔው ኦነግ በየቦታው ሲጨፈጨፍ እና ሲታረድ እንጀታቸው ቅቤ የጠጣ እንስኪመስል ድረስ ቁጭ ብለው ተሳልቁበት፡፡ እህቶቻችን ለትምህርት ከተላኩበት ታግተው ሲወሰዱ እና ደብዛቸው ሲጠፋ ከሕዝብ ጋራ ሆነው ከመፈለግ እና ከማፋላለግ ይልቅ ብአዴንናዊያን በልባቸው ድሮስ ማን ሂዱ አላቸው ብለው ተሳልቀውብናል፡፡በይፋ ባይሉት ድርጊታቸው ይናገራል፡፡ ፋረንጅ Actions speak louder than words ይል የለ፡፡  ወገን የወገን ያለህ እያለ ሲጮህ ጭራሽ ለአራጆቹ ካባ ሸለሙ ፡፡ እናተ ባትኖሩ ኖሮ አልቀን ነብር ብለው አሞኳሻቸው፡፡ እነ አገኘሁ ተሻገር በአማራ ሕዝብ ላይ ቀለዱበት ሳይሆን ተፀዳዱበት ነው መባል ያለበት፡፡ ገዱ ስለ ፋኖ ምን ነበር ያለው?

ይህ ሁሉ ሆኖ ተስፋ የማይቆረጠው የአማራ ሕዝብ በምራጫ ስንዱቅ ሂሳብ አወራርዳለሁ ብሎ ምርጫውን ሲጠብቅ ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ ተቀናቃኝ እና ተወዳዳሪ ያሉትን ድርጅቶች እና አባሎችን ማዋከብ ጀመሩ ፡ የሚገሉትን ገደሉ፡ የሚያስሩትን አሰሩ፡ የሚያሸማቅቁትን አሸማቀቁ፡፡ የምርጫ ሳጥን ሰረቀው እኛ ተመርጠናል አሉ ፡፡ በምርጫም ወቅት ሲቀሰቅሱ ይሉኝታ ቢስ እና ሆድ አደር የሆኑ የብአዴን አባሎች የአማራን ጨቋንኘት ከወያኔ እና ከኦነግ በተሻለ መልኩ ትንታኔ ሰጡ፡፡ ከሳምንት በፊት ለማ መገርሳ የብሄር ጭቆና አልነበረም ማለቱን እረሱት ዘነጉት፡፡ አዲሱን አለቆቻቸውን ለማስደሰት የዘረኝነት ካሴቱን ገለብጠው ማዘፋን ጀመሩ ፡፡ በአማራ ደም ተሳከረው በሬሳው ላይ ደነሱ ፡፡ አይ ዶክ ሂሩት አብይ ውለታሽን እንዴት ከፍሎሽ ይሆን፡፡

የአማራን ሕዝብ እንወክላለን ብለው ወንበር በያዙ በሳምንቱ ወያኔ ጀጋኑ ጀጋኑ መጫውት ጀመረች፡ ቅጥሎም አላማጣ ፡ ቆቦ ፡ ወልዲያ ፡ ደሴ ፡ ኮምቦለቻ እያለች ስትገሰግስ የሕዝብ ድምፅ እና ኮሮጆ ሰርቀው ተመረጥን ያሉ የብአዴን አመራሮች እግሬ አውጭኝ ብለው ሕዝብን ለወያኔ አረር ጥለው ፈረጠጡ፡፡ በዛም አልበቃም ብሎ የአማራ ሚሊሻ፣ ፋኖ፤ ልዩ ኃይሉ፣ እና መከላከያው ያለው በእዚህ ነው በእዛ በኩለ ነው እያሉ ለቀድሞ አለቆቻቸው ግልጋሎትም እየሰጡ ሰራዊቱን አስበሉት ፡፡ አይ ብአዴን በጭንቅ ሰአት አኩና አመሉን አረሳም ውርደት በኪሱ ቅሌት ቁርሱ አደረገ፡፡

ወያኔ አማራ ክልል ከገባች ጥይት እጠጣለሁ ያለው አገኘሁ ተሻገር ወያኔ አንኮበር ስትደርስ ከሌብነት አጋሮቹ ጋራ በመሆን 60 ሚሊዮን ብር ለቀምሴ አድርገው አገር ጥለው ሊሽበለሉ ተዘጋጁ ፡፡ ጥይት ከመጠጣት 10 ሚሊዮን ብር  መጠጣት ይሻላል አሉ ፡፡ የማፊያ ቦሱም አብይ ወይም ጎድ ፋዘር (Godfather) አላሳፈራቸውም ፡፡ እኔ እስካለሁ ድረስ ሺ አማራ ቢጫጫ በአንድ ሙቀጫ ብሎት አገኘሁ ተሻገር የአማራ ደም እየጠጣ ያስጠጣ አራት ኪሎ አስቀመጠው ፡፡ 

እንግዲህ ይህ ሁሉ ሲሆን በነ አሉ ደር ፀጥታ ነግሶ ነበር፡፡ በወለጋ አማራ ታረደ ዝም፡ በመተከል አማራ ታረደ ዝም፡ የኢትዮጵያን ስንደቅ የያዙ ተገደሉ ዝም፡ የአሉ መንደር ዝም አይነቅም ብሎ ዝም፡ መቼም ሌባ ሲስርቅ እንጂ ሲካፈል አይስማማም እንዲሉ እና የአማራ እናት እምባ ታከሎበት በድነገት ከሌቦቹ መንደር ጩኽት ተሰማ፡፡ ይህ ለምን እንደሆነ በግልፅ ባይታወቅም እራሱን የቻለ የፖለቲካ ቁማር እንዳለው የሚያሳብቁ ብዙ ነግሮች አሉት  ፡፡ ለምሳሌ የአማራ ሕዝብ በአረመኔዎች እየታረደ እና እየተፈናቀለ ባለበት ሰአት ለአማራ የሚያሳስበው ሕይወቱ ወይስ 60 ሚሊዮን ብር ብለን መጠየቅ እንችላለን ፡፡ ብሪቱስ ከተባለ ከንቲባዋ 2.2 ቢሊዮን አሹቅ ስታደርገው ሀቀኛ ሀቀኛ የተጫወተው አቶ ፀጋ  ምነው ከንቱማ / አዳነች አበቤን ባለሰማ አለፈ፡፡ መቼም ቢሆን የኦሮሙማ ዘረፋ ከወያኔ ጋራ በንፅፅር ቢቀርብ ወያኔ ስጥ ዘገነች እንጂ ዘረፋች አይባልም፡፡ ከጅምሩ ጠቅላዩ እራሳቸው ለምኜ ባመጣሁት ገንዘብ ማንም አያገባው ሲሉ ሌብነትን ሕጋዊ እንዳደርጉት መዘንጋት የለበትም፡፡ ከሌቦቹ መንደር ጩኽት በረከተ፡፡ ንፅህ ሰው አናውቅም ግን ሌባ ሌባን ፈነከት፡ ከማለት ሌላ ምን ይባላል፡

ማቲዎስ ወንጌል 6:24

በፖለቲካ ህግጋት ውስጥ የማይጣስ አንዱ ህግ የፓርቲ ታማኝነት ነው፡፡ይህም ከሚገለፅበት  መንገድ የፓርቲህን  ጉድፈቶች አንደባባይ አውጥተህ ባለመዘርገፍ ነው፡፡ ወይም በፓርቲ ውስጥ የሚነሱትን የአቋም ልዩነቶች እዛው ትፈታለህ እንጂ ለቡና ማጣጫ ወሬ አታድርጋቸውም ወይም ጦማሪ ቀጥረህ ለማህበራዊ ዜና አውታር ማድመቂያ አታውልም፡፡ የፓርቲን ሚስጢር መጠበቅ አንዱም የፖለቲካ ፓርቲ ታማኝነት መገለጫው ነው፡፡  ይህ ቀይ መሰመር ነው ፡፡ ይህን ቀይ መስመር አልፎ የወጣ አደገኛ አዳጋ ያጋጥመዋል ፡ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የፖለቲካው ጨዋታ ወይ ከኛ ወይ ከነሱ ነህ ፡፡ ዥዋዥዌ የለም

በአሉ መንደር የተሰለፉ ብአዴንናዊያን ከውትሮ በተለየ መልኩ የፈጠራቸውን የቀደሞ ኢሕዴግ የዛሬው ብልፅግና ፓርቲ በመተቸት ፣በመቃወም እና በመቃረን ላይ ይገኛሉ እየተባለ ነው ፡፡ ይህ በየዋህ አይን ሲታይ ጥሩ ነው ፡፡ ነገር ግን ከመተቸት፣ ከመቃወም እና ከመቃረን ቅጥሎ የሚመጣው አንድም ከፓርቲው መባረር አሊያም እራስን ከእኩይ ፓርቲ በማራቅ እና ቆመንለታል በድለነዋል ከሚሉት ሕዝብ ጋራ በመቆም ኢፍትሐዊ ያሉትን አሰራር በገሃድ መታገል ነው፡፡  በማቲዎስ ወንጌል 6:24 እንዲህ ይላል ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤  የነ አሉ ፖለቲካኞች ቪኤይትታቸውን እየሾፈሩ፡ በቪላ ቤታቸው እየኖሩ፡ ትኩስ ከበሪድ በውስኪ እያወራዱ ፡ ትኩሳት በተሰማቸው ቁጥር አሜሪካ እና ሲንጋፖር እየታከሙ የአማራ ሕዝብ ተበደለ፡ ፋኖ የአማራ ሕዝብ ነው ፡ ሰንደቅ የያዘ ተገድለ እያሉ ሲላዝኑ ድርጊታቸውን በጥንቃቄ አለመጠየቅ የዋህነት ነው ወይም እንደተባለው ዝንጉነት (short memory )ለባ መሆን ነው፡፡ በእንድኔ ግምት ይህ ድርጊታቸው  ከኦነግ እና ከወያኔ ጠላትነት ቢከፋ እንጂ አያንስም፡፡ ምክንያቱን የአማራን ሕዝብ በወያኔ እና በኦነግ ጥይት መገደሉ ሳያሰው እንሱም በስነ ልቦናም ጭምር እየገደሉት ስለሆነ ነው፡፡ እውነተኛ ሰዎች እና ለአማራ የሚቆረቆሩ ከሆነ ውለው ሳያድሩ አብይን ተሰናብተው የራሳቸውን ፓርቲ አቋቁመው ከሕዝባቸው ጋራ ለፍትህ ታግለው ሊያታግሉት ይገባል ፡፡ ያ እስኪሆን ድረስ ወገን አትዘናጋ የእንሱም ፖለቲካ የአሉ አሉ ነው፡፡ እኔም ብያልሁ  

ማሳሰቢያ

ይህ ፅሁፍ የተከተበው ብልፅግና ጉባኤውን ከማጠናቀቁ በፊት ነው ፡፡ ያላወጣሁትም ውጤቱን ለመጠበቅ ነው፡፡ አሁን የአሉ አሉ ፖለቲካ ቡድኖች ከእግዲህ ምን ቀረን የሚሉት ነገር ያለ አይመስለኝም ፡፡ ሕዝባቸውን ተቀላቅለው አዲስ ፓርቲ መስርተው ስርአቱን መታገል አለባቸው አቶም ፀጋም ተባሮ በለገስ ቱሉ ተተክቷል አሉ፡፡ የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም አሉ፡፡ በነካካ እጃችሁ ቅጥሉበት ፡፡ በዚህ ሆነ በእዛ መሞታችሁ ወይ መሰቃየታችሁ አይቀርም፡፡ ፍትህ፡ እክሉነት፡ ሰላም ፡ ያላት ኢትዮጵያ በጋራ እንገንባ